Policy Brief
ለስደተኞች እና ለስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰቦች የስራ እድል እና ማህበራዊ ትስስርን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና (TVET) ያለው ሚና፡፡ በኢትዮጵያ ከተካሄደው የተፅዕኖ ግምገማ (Impact Assessment) የተገኘ ማስረጃ
Getachew, Abis / Lisa Höckel / Jana Kuhnt / Abdirahman A. Muhumad / Armin von SchillerPolicy Brief (27/2023)
Bonn: German Institute of Development and Sustainability (IDOS)
DOI: https://doi.org/10.23661/ipb27.2023
Engl. Ausg. u.d.T.:
Improving employment and social cohesion among refugee and host communities through TVET: evidence from an impact assessment in Ethiopia
(Policy Brief 26/2023)
መንግስታት እና ለጋሾች በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና (ቴሙትስ) አማካኝነት የሥራ ዕድሎችን እና
ምርታማነትን የማሳደግ ከፍተኛ ምኞት አላቸው። ሥልጠናው በዋናነት የሥራ ገበያው የሚፈልገውን ሙያ
በማስተማር ብቃት ያለው የሰው ኃይል አቅርቦትን ማመቻቸት ይጠበቅበታል። እነዚሁ አካላት የቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ሥልጠና ከሥራ ስምሪት ባሻገር አካታችነትን፣ የፆታ እኩልነትን እና ማኅበራዊ ትስስርን (social
cohesion) በኅብረተሰቡ ውስጥ እንደሚያሻሽል ይገምታሉ።
የሥራ እድል ተደራሽነት ፤ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን በማጎልበት እንዲሁም ተፈናቃዮችን መልሶ
በማቋቋም ረገድ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። በስደት ረዥም ጊዜ መቆየት እና ወደሶስተኛ አገር የሚደረጉ የቋሚ
መፍትሄ እድሎች ማሽቆልቆል፤ የስደተኞች የመጀመርያ መዳረሻ አገሮች ውስጥ ማኅበራዊ ውህደት (local
integration) ፍለጋን አነሳስቷል። ባለፉት አስርት ዓመታት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ከፍተኛ ትኩረትን
የሳበው ከዚህ አንፃር ነው።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የእነዚህን መንግስታት እና ለጋሾች ምኞቶች ያሟላ ነው? በአጠቃላይ
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ላይ ያሉ ተጨባጭ ማስረጃዎች ውስን እና በአብዛኛው ወጥነት የሌላቸው
ናቸው። ከሥራና ከገቢ አንፃር ሲታይ ትንሽ አወንታዊ ውጤት እንዳለ መረጃዎች ቢጠቁሙም በአብዛኛው ውጤቶች
የሚታዩት ከመካከለኛ እስከ ረዥም ጊዜ (Medium and long term) ሲሆን፣ በአጠቃላይ ፕሮግራሞቹ ለረጅም ጊዜ
ሥራ አጦች በተሻለ ሁኔታ ይሰራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና በማኅበራዊ ትስስር ዙሪያ
ሊያመጣ የሚችለውን ውጤት በተመለከተ ትልቅ የእውቀት ክፍተት አለ። በፖሊሲው ከተቀመጠው የገንዘብ
መጠን እና ከሚጠበቀው ከፍተኛ ግምት አንፃር፣ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና የተቀመጠለትን ዓላማ እንዴት
እንደሚያሳካ መረዳት አስፈላጊ ነው።
በዚህ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ በጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጂአይዜድ) አማካኝንት በኢትዮጵያ
የተተገበረውን ሁሉን አቀፍ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና (TVET) ጥናት ውጤት አቅርበናል። በዚህ ፕሮግራም ስደተኞችን
ተቀባይ ሀገር ነዋሪዎች እና ስደተኞች በጋራ ስልጠናውን የተከታተሉ ሲሆን፣ ዓላማውም ማኅበራዊ ትስስርን
ማጎልበት እና የሥራ እድሎችን ማመቻቸት ነው።
የጥናቱ ውጤቶቹ እንደሚያመለክቱት፣ በማኅበራዊ ትስስር በኩል የታዩ ተፅእኖዎች በብዙ ገፅታ ጥሩ ቢሆኑም፣
ከገቢ እና ከሥራ እድል አንጻር ውጤቶቹ ዝቅተኛ እና የተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ ናቸው። አሃዛዊ እና አሃዛዊ
ያልሆኑ (quantitative and qualitative) ማስረጃዎች የሚጠቁሙት ስልጠናው የማኅበራዊ ትስስርን ለማሳደግ
እንደሚረዳ ነው፡፡ ከፕሮግራም ዲዛይን ወይም ከአፈጻጸም ችግሮች በላይ እንደ የሥራ እድሎች ውስንነት፣ የሕግ
ማቆዎች እና የፆታ እኩልነትን መሰረት ያደረገ እድል ያለመኖር እና የመሳሰሉ በመዋቅራዊ ችግሮች ስልጠናው
በስራ እድል ፈጠራ በኩል ውጤታማ እንዳይሆን ዋና መሰናክል ሆነው ይታያሉ።
የጥናቱ ዋና ዋና ምክረ ሃሳቦች፥
- የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (ቴሙትስ) ሲታቀድ ጥንቃቄ በተሞላበት ጥናት ማለትም፤ ከጉልበት
ገበያው አቅም እና ከህግ ማእቀፉ አንጻር በበቂ ሁኔታ መታየት አለበት፡፡ በተለይ የሥራ እድሎችን
ከመፍጠር አንጻር ይህ በጣም ወሳኝ ነው፡፡
- ማኅበራዊ ትስስርን ለማሻሻል ፤ አካታች የሆነ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ውጤታማ መሣሪያ ሆኖ
ይስተዋላል። ነገር ግን ማኅበራዊ ትስስር ፣ ከሥራ እድል ፈጠራ እንደ ተጨማሪ ውጤት ብቻ ሳይሆን
የስልጠናው ዋና ዓላማ ሆኖ የሚውሰድ ከሆነ፤ “ሌሎች የተሻሉ አማራጮች አልነበሩም ወይ?” የሚል
ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በተለይ ከሥራ እድል ፈጠራ እና ከገቢ አንጻር በተያያዘ ባለን ማስረጃ መሰረት ጥያቄውን
የበለጠ አስፈላጊ ያደርገዋል።
- አካታች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና (ቴሙትስ) መርሃ ግብር የሚያመጣውን ለውጥ በተመለከተ፣ ሰፋ ያሉ
ተጨማሪ ጥናቶችን ይፈልጋል። መሞላት ካለባቸው የእውቀት ክፍተቶች መካከል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና
በስደተኞች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ፣ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ እና አወንታዊ ተጽዕኖ፤ ሊያስከትል
የሚችለው ማኅበራዊ ተጽዕኖ፣ እንዲሁም በፆታ በኩል እና ከመካከለኛ እስከ የረዥም ጊዜ ያለው የሥራ እድል
ፈጠራ እና ገቢ ላይ የሚኖሩት ውጤቶች ይገኙበታል።
Contact
Cornelia Hornschild
Publication Coordinator
E-mail Cornelia.Hornschild@idos-research.de
Phone +49 (0)228 94927-135
Fax +49 (0)228 94927-130
Alexandra Fante
Librarian/ Open Access Coordinator
E-Mail Alexandra.Fante@idos-research.de
Telefon +49 (0)228 94927-321
Fax +49 (0)228 94927-130